1500 ችግኞችን በአንድ ጀንበር !
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች የ1500 ችግኞችን በአንድ ማለዳ የመትከል ግብ አሳኩ ።
የድርጅቱ ሰራተኞች ለ 2018 ዓ.ም የክረምት ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ቃሊቲ ወደሚገኘው የውሃና ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የተመሙ ሲሆን የያዙትን 1500 ችግኞችን በመትከል ግባቸውን አሳክተዋል።
በፕሮግራሙ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርሃን አበባው( ዶ /ር) ጨምሮ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የድርጅቱን መሠረተ ልማት የሚጠብቁት የፖሊስ አባላት ተግኝተዋል።
ሐምሌ 14 ፣ 2018 ዓ.ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments